በርዕደ መሬቱ ቀጣና ውስጥ ሆና ምንም ጉዳት ያልደረሰባት የቱርክ ከተማ አነጋጋሪ ሆናለች

በርዕደ መሬቱ ቀጣና ውስጥ ሆና ምንም ጉዳት ያልደረሰባት የቱርክ ከተማ አነጋጋሪ ሆናለች
ታትሟል

በቱርክ እና በሶሪያ ውስጥ የደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ በ10 ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።

በርካታ ከተሞች እንዳልነበሩ ሲሆኑ፣ ትንሽ ትልቅ ሳይባሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሕንጻዎችም ወደ ፍርስራሽነት ተቀይረዋል።

የአደጋው አካባቢ በሁለት አገራት ውስጥ በመቶዎቹ ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን አካባቢን የካለለ ሲሆን፣ ንዝረቱ ከዚያም አልፎ በጣም ርቀው በሚገኙ ቦታዎች ተሰምቷል ጉዳትም አድርሷል።

ነገር ግን በርዕደ መሬቱ ቀጠና ውስጥ የምትገኘው እና የመጀመሪያው ነውጥ ማዕከል ከነበረው ቦታ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ኧርዚን የተባለችው ከተማ ውስጥ አንድም ሰው አልተጎዳም፣ አንድም ሕንጻ አልፈረሰባትም። ለምን?