ሊቨርፑል ሲቲን በማሸነፍ መሪነቱን ያጠናክራል...? የ26ኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ሃላንድ እና ሳላህ
የምስሉ መግለጫ, ሃላንድ እና ሳላህ
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 4 ደቂቃ

በ26ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ። የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ወደ ማንቸስተር ተጉዞ ከአምናው ሻምፒዮን ከሲቲ ጋር ይጫወታል። ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ነጥብ ሊጥል ይችላል? ከሊቨርፑል በስምንት ነጥብ ዝቅ ብሎ ሁለተኛ ላይ የሚገኘው አርሰናል ደግሞ ዌስትሃምን በሜዳው ያስተናግዳል።

ክሪስ ሱቶን የሳምንቱን ጨዋታዎች የገመተ ሲሆን፣ ያልተጠበቁ ውጤቶች ሊመዘገቡ ይችላሉ ብሏል። ሊቨርፑል በመጠኑ መንሸራተት ገጥሞታል የሚለው ሱተን፣ የማንቸስተር ሲቲ ተከላካዮች ደግሞ ሊቨርፑልን እንዴት ሊያቆሙ እንደሚችሉ እርግጠኛ አይደለሁም ብሏል። ሱተን የጨዋታዎቹን ግምት ውጤት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

አርብ፣ የካቲት 14

ሌስተር ሲቲ ከብሬንትፎርድ

ሌስተር ሲቲ ከታኅሣሥ ወር መጀመሪያ ወዲህ በሜዳው አንድም ጨዋታ አሸንፎ አያውቅም። ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች ኪንግ ፓወር ላይ ተሸንፏል።

በመሆኑም ሌስተሮች በዚህ ጨዋታ የሆነ ነገር ማሳካት ከቻሉ እንደ ትልቅ ድል ነው የሚቆጠረው። ነገር ግን ብሬንትፎርድ ደግሞ እየተሻሻለ የመጣ ቡድን ስለሆነ ጨዋታውን ለማሸነፍ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል።

ግምት 1 - 2

ቅዳሜ፣ የካቲት 15

ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ

ኤቨርተን በደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ከማንቸስተር ዩናይትድ በላይ ተቀምጧል። አሁንም ይህንን ደረጃቸውን ያስጠብቃሉ ብዬ አስባለሁ። ኤቨርተኖች ኢሊማን ንዲያዬን በጉዳት ማጣታቸው አሳሳቢ ነው።ነገር ግን ዴቪድ ሞይስ ከመጡ በኋላ ቤቶ እያሳየ የሚገኘው መሻሻል አስደናቂ ነው።የግብ ዕድሎችን ይፈጥራል።

ይህ ጨዋታ ፉክክር ያለበት እና በጠባብ ውጤት የሚጠናቀቅ ሆኖ ይሰማኛል። ኤቨርተኖች ግብ ለማስቆጠር ዕድሎችን እየፈጠሩ ነው፤ በዚህኛው ጨዋታም ያሳኩታል ብዬ አስባለሁ።

ምንም ነገር ቢፈጠር ዩናይትድ ከሊጉ ላይወርድ ይችላል። ነገር ግን ሩበን አሞሪም ውጤት ይዘው መመለስ ይፈልጋሉ። ይህንን ለማሳካት የሚያስተካክሏቸው ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። ያ የማይሳካ ከሆነ ግን በደጋፊዎቹ ዘንድ የሚታየው ቅሬታ ይባባሳል። የኤሪክ ቴን ሃግ መባረር ያመጣው ለውጥ ምንድን ነው? የሚሉ ጥያቄዎች ይበረታሉ።

ግምት 1 - 1

ኤቨርተን ከማንቸስተር ዩናይትድ

በርንመዝ ከወልቭስ

ወልቭስ ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር እስከ መጨረሻው ደቂቃ ድረስ ተፋልሟል። ማቲዎስ ኩኒያም ድንቅ ግብ በማስቆጠር ብቃቱን አሳይቷል። ያንን ጥረታቸውን በዚህ ሳምንትም ይደግሙታል ብዬ አስባለሁ።

ቢሆንም ግን በርንመዝ በቀላሉ እጅ የሚሰጥ ቡድን አይደለም። በርንመዝ ለሻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ለመሆን የሚያስችለውን ቦታ ለማግኘት ከሚፎካከሩ ቡድኖች መካከል ነው። ያ ፉክክር ደግሞ በጣም አስፈላጊ ነው።

ግምት 2 - 1

አርሰናል ከዌስትሃም

ከሌስተር ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ 2 ግቦችን ማስቆጠሩን ተከትሎ ሚኬል ሜሪኖ ለአርሰናል ሁነኛ ሰው ሆኗል።

ተፎካካሪው ሊቨርፑል በአስቶን ቪላ ነጥብ መጣሉን ተከትሎ የአርሰናሉ አሠልጣኝ ይህንን ጨዋታ በልዩ ሁኔታ እንደሚያዩት ይጠበቃል።

ዌስትሃምን ካሸነፉ የነጥብ ልዩነታቸውን ወደ አምስት ዝቅ ያደርጋሉ። አሁን ባለው ሁኔታ ዌስትሃም መድፈኞቹን የሚያስቆሙ አይመስሉም።

ግምት 3 - 0

አርሰናል ከዌስትሃም

ፉልሃም ከክሪስታል ፓላስ

እነዚህ ሁለት ቡድኖች ለመገመት የሚከብዱ ናቸው። ማንኛውም ነገር ሊከሰት ይችላል። ክሪስታል ፓላስ ባለፈው ሳምንት በኤቨርተን ቢሸነፍም ጥሩ ተጫውቷል።

ፉልሃሞች ደግሞ ክራቭን ኮቴጅ ላይ ኖቲንግሃም ፎረስትን አሸንፏል። አሁን በሜዳቸው ለሁለተኛ ጊዜ ድል ያደርጋሉ ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ 2 - 1

ኢፕስዊች ከቶትንሃም

ኢፕስዊች ባለፈው ሳምንት ከአስቶን ቪላ ጋር በደንብ ተፎካክሯል። ነገር ግን ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ጨዋታዎችን ማሸነፍ ይኖርበታል።

ቶትንሃምን በውድድር ዓመቱ የመጀመሪያ ዙር አሸንፎታል። አሁንም ይፎካከራሉ ብዬ አስባለሁ። ነገር ግን ይህ ጨዋታ ለቶትንሃሙ አሠልጣኝ አንጄ ፖስቴኮግሉ ትልቅ ጨዋታ ነው። የጄምስ ማዲሰን እና የግብ ጠባቂው ቪካሪዮ ከጉዳት መመለስ ቶትንሃምን አግዞታል።

ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ ድንቅ ብቃት አሳይተዋል። በመሆኑም በዚህ ጨዋታ ሁለቱ ቡድኖች ነጥብ ይጋራሉ ብዬ አስባለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

ሳውዝአምፕተን ከበራይተን

ሳውዝአምፕተን ነጥብ ስለማግኘቱ ብዙም አይወራም። በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙት ሳውዝአምፕተኖች በየሳምንቱ እንደሚሸነፉ ገምቻለሁ። በዚህ ወቅት የሳውዝአምፕተን ደጋፊ መሆን በጣም ከባድ ነው። እኔም የእስከዛሬውን ግምቴን እደግመዋለሁ።

በዚህኛው ሳምንትም ድል እንደራቃቸው ይቀጥላሉ። ብራይተኖች ቼልሲን በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች ቢያሸንፉም ወጥነት ይጎድላቸዋል። ቢሆንም ግን ብራይተን ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ የታወቀ ነው። መገመት የሚጠበቅብኝ በምን ያክል የግብ ልዩነት የሚለውን ነው። በዚህ ጨዋታ ሳውዝአምፕተን ያሸንፋሉ ብሎ የሚገምት ይኖራል ብዬ አላስብም።

ግምት፡ 0 - 1

አስተን ቪላ ከቼልሲ

አስተን ቪላ ከቼልሲ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቼልሲ ውጤት እያጣ መጥቷል። አሠልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ደግሞ ጠንካራ ሆኖ መጨረስ አለባቸው።

ማሬስካ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ የቻምፕዮንስ ሊግ ቦታ ይዘው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል። ነገር ግን አሁን ባለው ሁኔታ መፈተናቸው አይቀርም። አስተን ቪላዎች የተሻሉ ይመስላሉ፣ ነገር ግን ከውጤት አንጻር ሲታይ ባለፉት አምስት ጨዋታዎች አንድ ተሸንፈው በአራቱ እኩል ወጥተዋል።

ሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ወደፊት ተጭኖ በመጫወት የተሻሉ ቢሆኑም፣ የግብ መረባቸውን መጠበቅ ግን ተስኗቸዋል። ስለዚህ ጉዳይ ለማሰብ የተወሰነ ጊዜ ወስጃለሁ። በዚህ ጨዋታ ቪላዎች ድል ያደርጋሉ። ይህ ደካማ ውጤት ከቀጠለ የቼልሲው አሠልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ጫና ይበረታባቸዋል።

ግምት፡ 2 - 1

እሑድ፣ የካቲት 16

ኒውካስል ከኖቲንግሃም ፎረስት

ይህ ጨዋታ ለሁለቱም ቡድኖች ከባድ ጨዋታ ነው። ሁለቱም ቡድኖች እስከ አራተኛ ባለው ደረጃ ውስጥ ሆነው ለማጠናቀቅ አንዱ ሌለውን ድል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

እኔ ኖቲንግሃም ፎረስት በፉልሃም የደረሰበትን ሽንፈት የሚቋጭበት እንዲሆን እፈልጋለሁ። እውነታው ግን እንደዚያ የሚሆን አይመስለኝም።

ኒውካስል ባለፈው ሳምንት በማንችስተር ሲቲ የደረሰበትን አሳፋሪ ሽንፈት ለመቀልበስ ሙሉ አቅሙን ይጠቀማል። አሌክሳንደር አይዛክ ልዩ ብቃቱን እንደሚያሳይ እጠብቃለሁ። አጠቃላይ ቡድኑም እንደሚነቃቃ እጠብቃለሁ።

ግምት፡ 2 - 0

ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል

ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል

ማንቸስተር ሲቲ በሳምንቱ አጋማሽ ወደ ስፔን አምርቶ በሪያል ማድሪድ ከቻምፕዮንስ ሊግ ውድድር ተሰናብቶ ተመልሷል። ጨዋታው የፔፕ ጋርዲዮላው ቡድን ደካማ እንቅስቃሴ ያሳየበት ነበር።

አብዛኛው እንቅስቃሴ ፔፕ ከሚታወቁበት አጨዋወት የራቀ ነው። አብዱኮዲር ኹሳኖቭ የቀኝ ተከላካይ ሆኖ መጨወቱ ብዙም ውጤታማ አይደለም። መሃል ላይ በርናርዶ ሲልቫ እና ጉንዶጋን ከኒኮ ጎንዛሌዝ ጋር የሚያደርጉት ጥምረት በተፈለገው ልክ አልሠራም።

ሪያል ማድሪድን የሚቋቋሙበት ብቃት አልነበራቸውም።

ሁል ጊዜ ሪያል ማድሪድ በዚህ ውድድር ተጠባቂ ነው። ነገር ግን ጨዋታው ከሲቲ ጋር ሲሆን ከፍተኛ ትንቅንቅ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። ነገር ግን ያ ፉክክር አልታየም።

ሊቨርፑሎች በሳምንቱ አጋማሽ በአስቶን ቪላ ተፈትነዋል። ይህ ፈተና ማንቸስተር ሲቲ ላይም ሊጠብቃቸው እንደሚችል መረዳት ይኖርባቸዋል።

ግምት፡ 1 - 3