ታይቶ በማይታወቅ ሙቀት እየተቃጠሉ ያሉት የአውሮፓ አገራት
ታይቶ በማይታወቅ ሙቀት እየተቃጠሉ ያሉት የአውሮፓ አገራት
ታትሟል
ባለፉት ሳምንታት በአውሮፓ አገራት ውስጥ የተከሰተው ከባድ ሙቀት ከዚህ በፊት ከታዩት ሁሉ የበለጠ እንደሆነ እየተነገረ ነው።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበረታ የመጣው የአየር ንብረት ለውጥ እየታየ ላለው ከባድ መቀት ምክንያቱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ እያደረሰ ያለው ጉዳት ቀላል የሚባል አይደለም።
ሙቀቱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት ምክንያት ከመሆኑ ባሻገር፣ በበርካታ አገራት ውስጥ ሰደድ እሳት እያስነሳ የመኖሪያ አካባቢዎችን ጭምር እያስለቀቀ ነው።



