የገንዘብ ለውጥ እና እጥረት ባስከተለው ቀውስ ውስጥ የሚካሄደው የናይጄሪያው ምርጫ
የገንዘብ ለውጥ እና እጥረት ባስከተለው ቀውስ ውስጥ የሚካሄደው የናይጄሪያው ምርጫ
ታትሟል
በናይጄሪያ ከሚካሄደው ምርጫ ቀደም ብሎ የአገሪቱ ማዕከላዊ ባንክ በአገሪቱ የመገበያያ ገንዘብ ላይ ለውጥ ማድረጉን ካሳወቀ በኋላ በጥሬ ገንዘብ እጥረት ምክንያት በአንዳንድ የአገሪቱ አካባቢዎች ቀውስ ተፈጥሯል።
ናይጄሪያውያን ገንዘባቸውን ለመለወጥ እና ከባንክ ገንዘብ ለማውጣት በመቸገራቸው ተቃውሞ እና ቁጣቸውን እያሰሙ ነው።
ይህ ደግሞ በበርካታ ከተሞች ገንዘብ ከባንክ ማውጣት ባልቻሉ ዜጎች ምክንያት አመጽ እና ግጭት እየተቀሰቀሰ ነው።
ታዲያ ይህ ሁኔታ በምርጫው ላይ እና በቀጣይ ቀናት በሚኖሩ የምርጫው ሂደቶች ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድር በበርካታ ናይጄሪያውያን ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል።



