የቤይሩት ፍንዳታ ተጎጂዎች ከሁለት ዓመት በኋላ ፍትህ እየጠየቁ ነው
የቤይሩት ፍንዳታ ተጎጂዎች ከሁለት ዓመት በኋላ ፍትህ እየጠየቁ ነው
ታትሟል
ከ200 በላይ ሰዎችን ለሞት የዳረገው የቤይሩት ወደብ ፍንዳታ ሁለት ዓመት ሆነው።
ፍንዳታው ከወደቡ አቅራቢያ ባሉ የመኖሪያ አካባቢዎች ባለ መጋዘን ውስጥ ለዓመታት አደገኛ ንጥረ ነገር ተከማችቶ እንዲቀመጥ ያደረጉ ባለሥልጣናትን ለደረሰው ጉዳት ነዋሪዎች ተጠያቂ ያደርጋሉ።
በደረሰው አደጋ ዙሪያ የተጀመረው ምርመራ ፖለቲከኞች የቻሉትን ሁሉ በማድረግ ቢያስቆሙትም፤ የፍንዳታው ሰለባዎች ቤተሰቦች ግን አሁንም ፍትህ እየጠየቁ ነው።
ለፍትህ እየታገሉ ከሚገኙት በርካታ የፍንዳታው ተጎጂዎች መካከል የኤሊያስ እናት አንዷ ናት።



