አርሰናል ከቼልሲ - ማን ያሸንፋል? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና የካራባኦ ዋንጫ ጨዋታዎች ግምቶች

ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 3 ደቂቃ

አርሰናሎች ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባለመቻላቸው ምክንያት ለፕሪሚየር ሊጉ ዋንጫ ያላቸው ተስፋ በእጅጉ ጠቧል።

በለንደን ደርቢ ከቼልሲ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ወደ ድል ይመለሱ ይሆን?

"በቼልሲ የአጥቂ መስመር መተማመን አልችልም። ኮል ፓልመር አቋሙ ወርዷል። ኒኮላስ ጃክስን በመጎዳቱ ፔድሮ ኔቶ የመሃል አጥቂ ሆኖ እየተጫወተ ነው" ሲል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ገልጿል።

"አርሰናልም በተመሳሳይ አጥቂ መስመር ችግር አለበት። ቼልሲ ይህንን ዕድል ይጠቀምበት ይሆን?" ሲል ጠይቆ "አይመስለኝም" ሲል ምላሹን ሰጥቷል።

ሱተን ይህንን የለንደን ደርቢን ጨምሮ የሳምንቱን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

ኤቨርተን ከ ዌስት ሃም

ጃሮድ ቦዌን እና ሞሐመድ ኩዱስ በጥሩ አቋም ላይ በመሆናቸው ዌስት ሃም ኳስ እና መረብ ያገናኛል።

አሠልጣኝ ዴቪድ ሞዬስ ከመጡ በኋላ ኤቨርተን ባለፉት ስምንት የሊጉ ጨዋታዎች ያለመሸነፍ ጉዞው ይቀጥላል።

ሞዬስ ባለፈው ክረምት ዌስት ሃምን ከለቀቁ በኋላ ኮንትራታቸው አለመራዘሙ ትክከክል አለመሆኑን የሚያሳዩበት ጨዋታ ይሆናል።

ግምት፡ 2 – 1

ኢፕስዊች ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

ኢፕስዊች በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማሳካት ቢፈልግም የሚሳካለት አይመስልም።

ከሁለት ሳምንት በፊት በኤፍኤ ዋንጫ ተገናኝተው በመለያ ምት ፎረስት አሸንፏል።

የኪራን ማኬና ቡድን በሊጉ ለመቆየት ያለፉትን ጥቂት ወራት ያላሳከውን ድል ማግኘት መጀመር አለበት።

ፎረስት ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ሲቲን ያሸነፈ ሲሆን፣ ይህንን ጨዋታ ለማሸነፍ የሚችሉ ድንቅ አጥቂዎችን ይዟል።

ግምት፡ 1 – 2

ማንቸስተር ሲቲ ከ ብራይተን

ይህ ለመገመት ከባድ የሆነ ጨዋታ ነው።

ብራይትን ያለፉትን አራት የሊግ ጨዋታዎች በማሸነፉ ለሻምፒዮንስ ሊግ ቦታ ለመፎካከር በቅቷል።

ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ከቻለም ከሲቲ በላይ መቀመጥ ይችላል።

ኦማር ማርሙሽን ያገኘነው ማንቸስተር ሲቲ ይበልጥ አስፈሪ መሆን ችሏል።

ግምት፡ 3 – 1

ሳውዝሃምፕተን ከ ዎልቨስ

ሳውዝሃምፕተን ባለፈው ሳምንት ጥሩ ተጫውቶ ጎል ማስቆጠር እንደሚችል ከሊቨርፑል ጋር በነበረው መርሃ ግብር አሳይቷል።

ማቲየስ ኩኛ በቅጣት ባይኖርም ዎልቭስ ከወራጅ ቀጣና የበለጠ ሊርቅ እንደሚችል የሚያሳይበት አጋጣሚ ነው።

በዚህ ሳምንት ዎልቭስ አሸንፎ ኢፕስዊች እና ሌስተር ከተሸነፉ ከወራጅ ቀጠና በዘጠኝ ነጥብ መራቅ ይችላል።

ግምት፡ 0 – 1

በርንመዝ ከ ብሬንትፈርድ

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ሲገኛኙ ብሬንትፈርድ ሁለት ጊዜ ተመርቶ 3 ለ 2 ማሸነፍ የቻለበት ድንቅ ጨዋታ ነበር።

በዕለቱ ብቻ ሳይሆን በርንመዝ ባለፈው ሳምንትም ከቶተንሃም ጋር ዕድለኛ አልነበረም።

ከሚያሳዩት እንቅስቃሴ አንጻር በዚህ ጨዋታ ዕድለኛ ሊሆኑ ይችላሉ።

ግምት፡ 2 – 1

እሑድ

አርሰናል ከ ቼልሲ

ይህ ጨዋታ ብዙ ግቦችን ላያስተናግድ ይችላል። አንድ ግብ ያስቆጠረ ቡድን ሊያሸንፍ ይችላል።

ዴክላን ራይስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በነበረው ጨዋታ በአጥቂ መስመር ላይ ተሰልፎ ድንቅ ሆኖ አምሽቷል። በዚህ ጨዋታም በተመሳሳይ ግብ እንደሚያስቆጥር እገምታለሁ።

ቼልሲ ባለፉት ሳምንታት ጥሩ መንቀሳቀስ አልቻለም። ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ያሸነፈውም በወራጅ ቀጣና የሚገኙት ቡድኖችን ነው።

ግምት፡ 1 – 0

ፉልሃም ከ ቶተንሃም

ቶተንሃም የተወሰኑ ተጫዋቾቹ ከጉዳት ቢመለሱም ከሐሙስ የዩሮፓ ሊግ ምን ያህል ያገግማሉ የሚለው የሚታይ ይሆናል።

ፉልሃም በሜዳው ወጥ መሆን ባይችልም በዚህ ጨዋታ ግምቱን እሰጣቸዋለሁ።

ግምት፡ 3 – 1

ሊቨርፑል ከ ኒውካስል ዩናይትድ

ይህ የካራባኦ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ ሲሆን፣ ዌምብሌይ ስታዲየም ላይ ይከናወናል።

ጨዋታው ኒውካስል ትልቅ ዋንጫ ለማሳካት ለዓመታት የጠበቀውን ጉዞ የሚያሳካበት ነው።

ቡድኑ ከአውሮፓውያኑ 2015 ወዲህ ሊቨርፑልን ካለማሸነፉም በላይ የሌዊስ ሃል እና የአንቶኒ ጎርደን መጎዳት ወደ ድል የመመለሳቸውን ነገር አጠራጣሪ ያደርገዋል።

ቲኖ ሊቭራሜንቶ በግራ መስመር ሃልን በመተካት ሞሐመድ ሳላህን ለማቆም ጥረት ለማድረግ ቢሞክሩም የሚሳካ አይመስልም።

ያለትሬንት አርኖልድ እና ኮኖር ብራድሌይ ወደ ሜዳ የሚገባው ሊቨርፑልም ጨዋታው ቀላል አይሆንለትም።

የመሃል ሜዳ የበላይነት በሚይዘው ቡድን የጨዋታው ውጤት የሚወሰን ይሆናል።

የቡድኑ በፒኤስጂ ከደረሰበት ሽንፈት ምን ያህል ያገግማል የሚለውም ትልቅ ጥያቄ ነው።

ግምት፡ 3 – 2

ሌስተር ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ሌስተር ዓመቱን ሙሉ በመከላከል ረገድ ችግር የነበረበት ሲሆን፣ አሁን ደግሞ የአጥቂው ከፍልም ሳስቷል።

ቡድኑ ባለፉት ጨዋታዎች ግብ የሚያስቆጥር አይመስልም።

ማንቸስተር ዩናይትድ ባለፈው ሳምንት ከአርሰናል ጋር በሁለተኛው አጋማሽ ተሻሽሎ ቢቀርብም ጥሩ የውድድር ዘመን እያሳለፈ አይደለም።

ከሳምንታት በፊት ሁለቱ ቡድኖች በኤፍኤ ካፕ ተገናኝተው ሃሪ ማጓየር ባለቀ ሰዓት ባስቆጠራት አጨቃጨቂ ግብ ዩናይትድ አሸናፊ ሆኗል።

ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅ ይሆናል።

ግምት፡ 1 – 1