እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ?

እስካሁን በኮሮናቫይረስ ያልተያዙ ሰዎች ለምን ሳይያዙ ቆዩ?
ታትሟል

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ በሁሉም አገራት የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለህመም፣ ከተወሳሰበ የጤና ችግር እና ለሞት ዳርጓል።

ይህ በሽታ ከተከሰተ ሁለት ዓመት ያለፈው ሲሆን ከመተላለፊያ መንገዶቹ አመቺነት የተነሳ በአጭር ጊዜ መላውን ዓለም አዳርሷል።

አንዳንዶች እንዲያውም አብዛኛው የዓለም ሕዝብ በበሽታው የመያዝ ዕድል አለው ይላሉ።

ከወረርሽኙ የስርጭት ፍጥነት እና ስፋት አንጻር በርካቶች ለቫይረሱ የተጋለጡ ቢሆንም፣ ተጋላጭ ቢሆኑም በርካቶች አስካሁን በሽታው አልያዛቸውም ይባላል።

ለዚህ ምክንያቱ ምንድን ነው?