ፍልስጤማውያንን ያስጨነቀው መፈናቀል እና የእስራኤል ዕቅድ
ፍልስጤማውያንን ያስጨነቀው መፈናቀል እና የእስራኤል ዕቅድ
ታትሟል
የእስራኤል ወታደሮች በቅርቡ ቤታቸውን ለማፍረስ መዘጋጀታቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ በዌስት ባንክ የሚኖሩ ፍልስጤማውያን ጭንቅ ውስጥ ናቸው።
ይህ የእስራኤል ዕቅድ ተግባራዊ የሚሆን ከሆነ በአካባቢው በአስርት ዓመታት ውስጥ በጣም ከፍተኛውን መፈናቀል እንደሚያስከትል የመንግሥታቱ ድርጅት አመልክቷል።
በዌስት ባንክ ፈቃድ ሳያገኙ የተገነቡ ናቸው ያለቻቸውን ቤቶች እስራኤል ከአሁኑ ማፍረስ ጀምራለች። ይህ ሂደት በሁላችንም ዘንድ ይደርሳል በሚል በርካታ ፍልስጤማውያን በፍርሃት ውስጥ ናቸው።



