ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ከፍተኛ ሙቀት በነበረባት አውሮፓ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ንፋስ ለ13 ሰዎች ሞት ምክንያት ሆነ
መካከለኛው እና ደቡባዊ አውሮፓ ዝናብ በቀላቀለ ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በመመታቱ ሦስት ሕጻናትን ጨምሮ ቢያንስ የ13 ሰዎች ሕይወት አልፏል።
የአብዛኛዎቹ ሕይወት ያለፈው በዛፎች መውደወቅ ምክንያት ነው። በጣሊያን፣ ኦስትሪያ እንዲሁም በፈረንሣይ ኮርሲካ ደሴት ጉዳቱ መድረሱ ተዘግቧል።
በደሴቲቱ ከባድ ዝናብ እና ንፋስ አደጋ አድርሷል። ጣሊያን ቬኒስ የሚገኘው የሴንት ማርክ ቤተ መቅደስ ደወል ግንቡ መውደቁ ተዘግቧል።
አውሎ ንፋሱ በአውሮፓ ለሳምንታት የዘለቀውን የሙቀት ማዕበል እና ድርቅ ተከትሎ ተከስቷል።
በኮርሲካ በሰዓት እስከ 224 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ንፋስ ዛፎችን ነቅሎ ተንቀሳቃሽ ቤቶችን ከጥቅም ውጭ አድርጓል።
የ13 ዓመቷ ልጅ ዛፍ ወድቆባት ሕይወቷ ማለፉን ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።
በተመሳሳይ ሁኔታ አንድ ግለሰብም ሕይወቱ ማለፉን ተናግረዋል። አንድ የዕድሜ ባለጸጋ መኪናቸው ውስጥ ሕይወታቸው ማለፉንም አስታውቀዋል።
ሌሎች ሁለት ሰዎች በባሕር ዳርቻ ላይ ሕይወታቸው አልፏል።
በአውሎንፋስ የደረሰውን ጉዳት ለመመርመር ኮርሲካ የደረሱት የፈረንሳዩ የአገር ውስጥጉዳይ ሚኒስትር ጄራልድ ዳርማኒን የተጨማሪ ስድስተኛሰው ሕይወት ማለፉንተናግረዋል።
በደርዘንየሚቆጠሩ ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የዓይንእማኞች አውሎ ንፋሶቹ ያልተጠበቁ እንደነበሩ እና ምንም ማስጠንቀቂያ እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል።
የሬስቶራንትባለቤት የሆነው ሴድሪክ ቦኤል ለሮይተርስ የዜና ወኪል "እንደዚህ ዓይነት ግዙፍአውሎ ንፋስ አይተን አናውቅም” ብለዋል።
በፈረንሳይአንዳንድ ደቡባዊ አካባቢዎች የኃይል መቆራረጥ ሲያጋጥም የማርሴይ ከተማ ጎዳናዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል።
በኦስትሪያዋካሪንቲያ ሐይቅ አቅራቢያ በወደቀ ዛፍ ምክንያት የሁለት ታዳጊሴቶች ሕይወት አልፏል።
በተመሳሳይሁኔታ ተጨማሪ ሦስት ሰዎች መሞታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
በጣሊያኗቱስካኒ ክልል ሁለት ሰዎች በተለያየ ቦታ በወደቀ ዛፍ ሕይወታቸው አልፏል።
በቬኒስሴንት ማርክ አደባባይ የካፌ ዣንጥላዎች የተነቃቀሉ ሲሆን የካቴድራሉ የደወል ማማ ጡብ መውደቁ ተነግሯል።
በቱስካኒእና በሊጉሪያ በስተሰሜን የሚገኙ የባሕር ዳርቻመዝናኛዎች በአውሎ ንፋሱ ተጎድተዋል።
በደቡባዊጣሊያን ደግሞ የሙቀት ማዕበሉ ቀጥሏል። በሲሲሊ እስከ 40 ሴንቲግሬድ የሚደርስ ሙቀት ተመዝግቧል።
በአልጄሪያበተከሰተተ የደን ቃጠሎ ቢያንስ 38 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።
በብዙየአውሮፓ አገራት ከፍተኛሙቀት እና ደረቅ የአየር ሁኔታ ለሳምንታት ተመዝግቧል።
ባለፉትጥቂት ዓመታት ከፍተኛ የሙቀት ሞገድ እና አውሎ ንፋሶችን ጨምሮ አስከፊ የአየር ሁኔታዎች በተደጋጋሚ ተከስተዋል።
ይህም የሰው ልጅ በተፈጥሮ ላይ ባደረሰው ጉዳት ሳቢያ በተባባሰው የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት መከሰቱ ተነግሯል።
ከኢንዱስትሪዘመን ጅማሮ አንስቶ ዓለም በ1.1 ሴንቲ ግሬድ ገደማ ሙቀቷ ጨምሯል።
መንግሥታት ከፍተኛየሆነ የልቀት መጠን መቀነስ ካላደረጉ የሙቀቱ መጠን እየጨመረ ይሄዳል።