አንድ አገር የነበሩትን ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያን ለ70 ዓመታት ያፋጠጣቸው ምንድን ነው?

አንድ አገር የነበሩትን ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያን ለ70 ዓመታት ያፋጠጣቸው ምንድን ነው?
ታትሟል

ምንም እንኳን ፊትለፊት የሚደረግ ጦርነት ባይኖርም ሰሜን እና ደቡብ ኮሪያ ላለፉት ሰባ ዓመታት ጦርነት በሚባል ሁኔታ ውስጥ ናቸው።

ኮሪያን ለሁለት የከፈለው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ ለስሙ የተኩስ አቁም ስምምነት ፈርመዋል፣ ነገር ግን ከዛሬ ነገ ሊፈነዳ ይችላል በሚባል ፍጥጫ ውስጥ ለሰባት አስርት ዓመታት ቆይተዋል።

አሁን ደግሞ ዘመኑ ያፈራቸው ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎች ሁለቱን ወገኖች ወደ ባሰ ፍጥጫ ክትቷቸዋል።

ለመሆኑ ሁለቱ ኮሪያዎች እዚህ ላይ እንዴት ደረሱ?