ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ማንቸስተር ሲቲ ከቼልሲ እና ሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት
ማንቸስተር ሲቲ በፕሪሚየር ሊጉ ያለፉትን አምስት ጨዋታዎች አልተሸነፈም። ቼልሲን ቅዳሜ ካስተናገደ በሏላ ከአርሰናል፣ ኒውካስል እና ሊቨርፑል ጋር በተከታታይ ይጫወታል።
"የሲቲን ትክክለኛ ደረጃ ልናውቅ ነው" ብሏል የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን።
"ቀላል ጨዋታዎችን ሲያከናወኑ ቢቆዩም ቀጣዮቹ ጨዋታዎች የውድድር ዓመቱን የሚወስኑ ናቸው። ወደ ሻምፒዮንስ ሊግ ጥሎ ማለፍ ካለፉ በቀጣይ ወር የሚኖራቸውን የጨዋታ መርሃ ግብር የበለጠ ከባድ ያደርገዋል" ሲል አክሏል።
ሱተን ማንቸስተር ሲቲ ከቼልሲ የሚያደርጉትን ጨምሮ ቀሪዎቹን የፕሪሚየር ሊጉን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።
በርንመዝ ከኖቲንግሃም ፎረስት
ይህ ሁለቱም በጥሩ አቋም ላይ የሚገኙ ክለቦችን የሚያፋልም መርሃ ግብር ነው።
በርንመዝ ባለፈው ሳምንት ከኒውካስል ጋር ድንቅ አቋም በማሳየት አሸንፏል።
ይህ ጨዋታ በአቻ ውጤት የሚጠናቀቅበት ዕድል ከፍተኛ ቢሆንም ድሉን ለበርንመዝ እሰጣለሁ።
ግምት፡ 2 – 1
ብራይተን ከኤቨርተን
ኤቨርተን የተከላካይ ክፍሉ ደካማ የሆነውን ቶተንሃምን 3 ለ 2 ማሸነፍ ቢችልም የዴቪድ ሞዬሱን ቡድን መገመት ከባድ ነው።
ከሜዳው ውጭ ማንቸስተር ዩናይትድን ያሸንፍ እንጂ ብራይተንም ሊገመት የሚችል ቡድን አይደለም።
ኤቨርተን ከዚህ ጨዋታ ውጤት ለማግኘት ብዙ መሥራት ይጠበቅበታል።
ቡድኑ ቶተንሃም ላይ ሦስት ጎሎችን ቢያስቆጥርም ኳስ እና መረብ በማገናኘት በኩል ክፍተት አለበት።
ግምት፡ 2 – 0
ሊቨርፑል ከኢፕስዊች
የኢፕስዊች ደጋፊዎች ብዙ ርቀት ተጉዘው ሽንፈት ተከናንበው የሚመለሱበት ጨዋታ ነው።
ሊቨርፑል ጎሎችን በማስቆጠር በኩል ችግር ባይኖርበት በተለያዩ ውድድሮች መሳተፉ ሊያዳክመው ይችላል።
ግምት፡ 3 – 0
ሳውዝአምፕተን ከኒውካስል
ኒውካስል ባለፈው ሳምንት በበርንመዝ 4 ለ 1 መሸነፉን ተከትሎ ከሊቨርፑል ጋር ይኖረዋል ተብሎ ሲወራ የነበረው ፉክክር በፍጥነት ተቀዛቅዟል።
ቡድኑ ወደ ድል የሚመለስብትን ጥሩ አጋጣሚ አግኝቷል።
ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ኖቲንግሃም ጋር ጥሩ መፎካከር የቻሉት ሳውዝአምፕተኖች በጨዋታዎቹ ከመሸነፍ ግን አልዳኑም።
ቡድኑ የመወርዱ ነገር ባያጠራጥርም ትኩረቱ በዝቀተኛ ነጥብ የወረደ ቡድን በመሆን ታሪክ ላለማስመዝገብ ነው።
ይህንን ታሪክ ላለመጻፍ ከሚቀጥሉት 16 ጨዋታዎች 11 ነጥብ ማግኘት ይኖርባቸዋል።
ግምት፡ 0 – 2
ዎልቭስ ከአርሰናል
ዎልቭስ ባለፈው ሳምንት በቼልሲ ከተሸነፈ በኋላ አጥቂው ማቲያስ ኩኛ ባሳየው ድርጊት አሰልጣኙ ቪቶር ፔሬራ ደስተኛ አልመሆናቸውን ገልጸዋል።
ዘንድሮ በርካታ ጎሎችን ያስቆጠረው አጥቂው ትችቱ ሊያነቃቀው ወይንም ደግሞ ሊሰብረው ይችላል።
መድፈኞቹ ጉልበት ለመሰብሰብ በሚል የብራዚላዊያኑን የሳምባ ሙዚቃ በልምምድ ሜዳ ሲያጫውቱ እንደነበር አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አስታውቋል።
አሰልጣኙ አዳዲስ ሃሳቦችን በመሞከር ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፈው ሳምንት 2 ለ 0 ቢመራም ከአስቶን ቪላ ጋር ነጥብ ለመጋራት ተገዷል። በዚህ ሳምት ግን ወደ አሸናፊነት ይመለሳል።
ግምት፡ 0 – 2
ማንቸስተር ሲቲ ከቼልሲ
ሲቲ በተከታታይ በሊጉ ሦስት ነጥቦችን መሰብሰቡ እየተመሰለ ነው ቢያስብለውም በሻምፒዮንስ ሊጉ በፒኤስጂ የደረሰበት ሽንፈት ክፍተቱን ያሳየ ሆኗል።
ያስፈረሟቸው ተጫዋቾች ብዛት አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ያለባቸውን ክፍተት ማሳያ ሊሆን ይችላል።
ሲቲ በሻምፒዮንስ ሊጉ አጣብቂኝ ውስጥ ከመግባቱም በላይ በሊጉም በተከታታይ ጠንካራ ጨዋታዎች ይጠበብቁታል።
ኮል ፓልመር እና አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ወደ እናት ቀጣሪያቸው ሜዳ የሚመለሱበት መርሃ ግብር ነው።
ይህ እስከ አራት ባሉት ደረጃዎች ለማጠናቀቅ በሚደረገው ፉክክር ትልቅ ተጽዕኖ የሚኖረው ጨዋታ ይሆናል።
ግምት፡ 2 – 1
ክሪስታል ፓላስ ከብሬንትፎርድ
ፓላሶች ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ሦስቱን አሸንፈው በሁለቱ አቻ ተለያይተዋል።
በአቋም በኩል ካየነው ብሬንትፎርድ ባለፈው ሳምንት ከሊቨርፑል ጋር አስደናቂ መሆኑን አሳይቷል።
በዚህ ጨዋታም ጎል ማስቆጠር ቢችሉም አሸንፈው መውጣት ግን አይችሉም።
ግምት፡ 1 – 1
ቶተንሃም ከ ሌስተር
ቶተንሃም በስድስት የሊጉ ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ቢያገኝም ከሌስተር አንጻር ሲታይ የተሻለ ነው።
አሰልጣኝ አንጅ ፖስቴኮግሉ ጫና ውስጥ ይገኛሉ። በዚህ ጨዋታ ከተሸነፉ ደግሞ ጫናው ይበረታል።
ሁለቱ ቡድኖች በውድድር ዓመቱ መጀመሪያ አንድ አቻ ቢለያዩም ይህንን ጨዋታ ቶተንሃም ያሸንፋል።
ግምት፡ 4 – 1
አስቶን ቪላ ከዌስት ሃም
ቪላ ጥሩ የሚባል የውድድር ዘመን እያሳለፈ አይደለም።
ቡድኑ በሻምፒዮንስ ሊግ ከሞናኮ ጋር ሲጫወት ጆን ዱራንን እና ኦሊ ዋትኪንስን ለማጣመር የተደረገው ሙከራ ፍሬያማ አልሆነም።
ሁለቱም ተጫዋቾች ቡድኑን በሚጠቅም መልኩ አብረው ውጤታማ ሚሆኑበትን መንገድ መፈለግ ይኖርባቸዋል።
ይህ ለቪላ ወሳኝ የውድድር ዓመቱ ጊዜ ሲሆን ዌስት ሃምን ማሸነፍ ይችላል።
ግምት፡ 2 – 1
ፉልሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ
አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ቡድናቸው ከዚህ ቀደም ከነበሩት የማንቸስተር ዩናይትድ ቡድኖች "ምናልባትም ደካማው ሳይሆን አይቀርም" ያሉበትን አስተያየት ተገቢ አለመሆኑን አስታውቀዋል።
ፉልሃም ወደ ፊት ሲሄድ ከማንቸስተር ዩናይትድ በተሻለ መንቀሳቀስ እንደሚችል ደጋግሞ አሳይቷል።
እንዲህ አይነቱ አጨዋወት ለዩናይትድ እንደሚመች ደጋግመን ተመልክተናል። ይህን ለማድረግ ግን በጥሩ አቋም ላይ መሆን አለባቸው። በዚህ ረገድ የትኛውን ዩናይትድን እንደምንመለከት ለመገመት ከባድ ነው።
ግምት፡ 2 – 1