በርካታ ተመልካችን እያገኘ የመጣው በጥፊ የመመታታት ውድድር

በርካታ ተመልካችን እያገኘ የመጣው በጥፊ የመመታታት ውድድር
ታትሟል

ይህ በጥፊ የመቀጣቀጥ 'ስፖርት' በፓኪስታኗ የፑንጃብ ግዛት ውስጥ እጅግ ተወዳጅ ነው።

ካባዲ በመባል የሚታወቀው ይህ የጥፊ ውድድር ከፓኪስታን ባሻገር በደቡብ እስያ ውስጥም የተለመደ እና ብዙ ታዳሚ ያለው ነው።

በውድድሩ ተጫዋቾቹ ተጋጣሚያቸውን ባጮሉ ቁጥር ተጨማሪ ነጥብ ይቆጠርላቸዋል። ይህ ስፖርት በተለይ በበዓላት ወቅት ተዘውታሪ እየሆነ መጥቷል።