ነፍሰ ጡሯ የአዳማዋ ቴኳንዶ እና ኤሮቢክስ አሰልጣኝ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ነፍሰ ጡሯ የቴኳንዶ እና ኤሮቢክስ አሰልጣኝ
ነፍሰ ጡሯ የአዳማዋ ቴኳንዶ እና ኤሮቢክስ አሰልጣኝ
ታትሟል

የአዳማ ነዋሪ የሆነችው ሽልማት ሲሳይ የኤሮቢክስ እና የቴኳንዶ አሰልጣኝ ናት።

የሦስት ልጆች እናት የሆነችው ሽልማት አራተኛ ልጇን የስምንት ወር ነፍሰ ጡር ናት።

እርግዝናዋ ግን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ማሰልጠንም እንዳልከለከላት ትናገራለች።

ሽልማት ስፖርት ማዘውተሬ ምጤን አቅልሎታል ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።