ኮሮናቫይረስ፡ ህንዳዊው ኮቨድ-19ን ለመከላከል አካላዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስችል ሞተር ሳይክል ሠራ

ታትሟል

በህንድ አንድ ግለሰብ የኮሮናቫይረስ ቢያስጨንቀው ልጁን ከትምህርት ቤት ለመውሰድ እንዲያስችለው አካላዊ ርቀትን የጠበቀ ሞተር ሳይክል ሰርቷል። ሞተር ሳይክሉን ከተሰባበሩ ብረቶች በእሱና በልጁ መቀመጫ መካከል የአንድ ሜትር ልዩነት እንዲኖረው አድርጎ ነው የሠራው።