ጥቁሩ ሳጥን፤ በአውሮፕላኖች ላይ የሚደርስ አደጋን ለሚደረግ ምርመራ ጠቃሚ መረጃን የሚይዝ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ነው።

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, ጥቁሩ ሳጥን፤ በአውሮፕላኖች ላይ የሚደርስ አደጋን ለሚደረግ ምርመራ ጠቃሚ መረጃን የሚይዝ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ነው።
ታትሟል

ጥቁሩ ሳጥን ወይም በአየር ትራንስፖርት ባለሙያዎች ዘንድ የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ተብሎ የሚታወቀው ቀለሙ ግን ጥቁር አይደለም። ይህ የመረጃ ሳጥ ን ከአደጋ በኋላ በቀላሉ ለማግኘት እንዲቻል ቀለሙ ደማቅ ብርቱካናማ ነው። መጠኑም የጫማ መያዣ ካርቶን የሚያክል ሲሆን፤ በውስጡም ሁለት ክፍሎችን ይዟል። እነሱም የበረራ መረጃ መመዝገቢያ እና የበረራ ክፍል ድምፅ መቅጃ ናቸው። የበረራ መረጃ መመዝገቢያው የአየር ሙቀት መጠን፣ ፍጥነት፣ ከፍታ፣ የነዳጅ መጠንና የመሳሰሉትን የ25 ሰዓታት መረጃ ይይዛል። የበረራ ክፍል ድምፅ መቅጃ የበረራ ሠራተኞችን ንግግር፣ የአውሮፕላኑን የሞትር ድምፅና ከአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር የተደረጉ ምልልሶችን ጨምሮ ሁሉንም ድምፆች ቀርፆ ይይዛል። የድምፅ መቅጃው ለሁለት ሰዓታት ያህል ድምፅ የሚቀዳ ሲሆን መርማሪዎች አደጋው በቴክኒክ ችግር ይሁን በሰዎች ስህተት መከሰቱን ለመለየት ያግዛል። በጥቁሩ ሳጥን ውስጣዊ ክፍል መረጃውን ማስቀመጫ ሰሌዳ በሙቀት ማገጃ ተሸፍኖ ይገኛል። ይህም እስከ 1000 ዲግሪ ሴሊሺየስ የሚደርስ ሙቀትን ለአንድ ሰዓት የሚቋቋም ሲሆን በጨዋማና በሌሎች ፈሳሾች ውስጥ ሳይበላሽ እንዲቆይ ተደርጎ የተሠራ ነው። ሳጥኑ ውሃ ውስጥ ከገባበት ጊዜ አንስቶ እንደ አውሮፕላኑ ዓይነት ከ30 እስከ 90 ቀናት ድረስ የማይቋረጥ፤ ያለበትን ቦታ አመላካች የአልትራሳውንድ ምልክት ይሰጣል። አንዳንዶች ጥቁሩ ሳጥን መረጃዎችን በሳተላይትን በኩል ወዲያው ማስተላለፍ ቢችል ከአደጋ በኋላ ሳጥኑን በመፈለግ የሚጠፋውን ጊዜ ያስቀራል ይላሉ።