ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ከዝነኛ አዝማሪነት ወደ አርሶ አደርነት የተሸጋገረው ማሲንቆ ተጫዋች
ታትሟል
ሰጠ ዘበኛ በላስታ ላሊበላና አካባቢው ዝነኛ አዝማሪ ነው። "ባውሽ ባውሽ ላስታ ላግኝሽ" የሚል አልበም አሳትሞ ብዙ አድናቂዎችን ሰብስቧል።
በላስታና አካባቢው ሠርግና ሌላ የደስታ ድግስ ያለ ሰጠ አይደምቅም ነበር። የላስታ ላሊበላ የባሕል ቡድን አባል በመሆን ለሰባት ዓመታት የአካባቢውን ባሕል አስተዋውቋል።
ከሁለት ዓመት በፊት የተከሰተው ኮሮናቫይረስ ግን የሰጠን ሕይወት በብዙ ዓመታት ወደኋላ መልሶታል። ወደ ላሊበላ የሚተመው ጎብኚ ሙሉ በሙሉ በመቆሙ ሰጠ ስራ አጥ ሆነ።
በትግራይ ተቀስቅሶ ወደ አማራ ክልል የተሸጋገረው ጦርነት ደግሞ ሕይወቱን ይበልጥ አመሰቃቀለው።
ቤተሰቡን ለማስተዳደር አማራጭ ያለውን መረጠ።
አርሶ አደር መሆን።