በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ከባድ ዋጋ የከፈሉት ሴቶች

ታትሟል

የኢንዱስትሪ ከተማ በሆነችው ኮምቦልቻ የሕወሓት ወታደሮች በቆዩባቸው ከ30 በላይ ቀናት በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል።

አስገድዶ መደፈር በከተማዋ በስፋት ተፈጽሟል። መገለልን በመፍራት የደረሰባቸውን ጾታዊ ጥቃት ሪፖርት ያላደሩ እንዳሉ ይገመታል። እስካሁን በተደረገው ጥናት በከተማዋ 35 ሴቶች በወታደሮቹ መደፈራቸውን ሪፖርት አድርገዋል።