ኔቶ የዩክሬንን ፍላጎት እንዳያሟላ ያደረገው የሩሲያ ማስጠንቀቂያ

ታትሟል

የምዕራባውያን የመከላከያ ትብብር የሆነው የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት ወደ የምሥራቅ አውሮፓ አገራት መስፋፋቱ ለብሔራዊ ደኅንነቷ ስጋት እንደሆነ በመግለጽ ሩሲያ ተቃውሞዋን ስትገልጽ ቆይታለች።

በዚህም ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያላት ፍላጎት ሩሲያ ለከፈተችው ወረራም አንዱ ምክንያት እንደሆነ ይነገራል። ወረራውን ተከትሎም የኔቶ አገራት ዩክሬንን ለመከላከል ሲሉ ወደ ጦርነቱ ይገባሉ ተብሎ ስጋት ውስጥ ተገብቶ ነበር።

ነገር ግን ኔቶ በዚህ ጦርነት ውስጥ በቀጥታ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌለው ገልጿል። ሩሲያም ኔቶም ሆነ አባሎቹ በቀጥታ ለመሳተፍ ከሞከሩ "በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ እርምጃ" እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።