በቆሎን ወደ ቢራ የቀየረው ወጣት ኤርሚያስ ዋቅሹማ

ታትሟል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ተማሪ የሆነው ኤርሚያስ ዋቅሹማ ከበቆሎ ውስኪና ቢራ ማምረቱን ይናገራል።

የሚማርበት ዩኒቨርስቲ ከሄኒከን ፋብሪካ ጋር በፈጠረለት ትስስር ያመረተውን ምርት ለዩኒቨርስቲው እና ለቢራ ፋብሪካው ኃላፊዎች ማቅመስ ችሏል።

ኤርሚያስ ዋቅሹማ፣ የፈጠራ ሥራውን በአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ለማስመዝገብ እየሠራ መሆኑን ተናግሯል።