ጉዬ አዶሎ፡ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር በመወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል"

ታትሟል

የበርሊን ማራቶን አሸናፊው አትሌት ጉዬ አዶላ "ቀነኒሳን ከመሰለ ጀግና ጋር መወዳደሬ ትልቅ ደስታ ይስማኛል" ሲል ተናገረ።

አትሌት ጉዬ ውድድሩ እንደ አጠቃላይ ቆንጆ ነበር ያለ ካለ በኋላ፤ "በሰዓቱ ደስተኛ ባልሆነም አንደኛ በመውጣቴ ደስ ብሎኛል" ብሏል።

በውድድሩ ጥሩ ሰዓት ያልተመዘገበው በበርሊን የነበረው ከፍተኛ ሙቀት እንደምክንያት ያነሳው አትሌቱ፤ በውድድር ላይ የሚያጋጥሙ ስህተቶችን በማራም በቀጣይ ውድድር የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

"የማስበው የኤሊዩድ ሪኮርድ መስበር ነው"

ትናንት በተካሄደው የበርሊን ማራቶን ላሌኛው ክስተት የሆነው ኢትዮጵያዊው ወጣት አትሌት አባቴ ታዱ ነው።

አትሌት አባቴ ታዱ 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን፤ "እንደ ጉዬ አዶላ እና ቀነኒሳ በቀለ ያሉ ልምድ ያላቸው ተወዳዳሪዎች ነበሩ። ከእነርሱ ጋር ተወዳድሬ ልምድ በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ" ብሏል።

አትሌት አባቴ ታዱ "የወደፊት እቅዴ በደንብ ሰርቼ ይሄን የኤሊይድ ኪፕቾጌን ሪኮርድ መስበር አለብኝ ብዬ ነው ማስበው" ብሏል።