ከዓሳ ነባሪ ሆድ 1.5 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ በረከት ያገኙት ዓሳ አስጋሪዎች

ታትሟል

የመናውያን ዓሳ አስጋሪዎች በኤደን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ አንድ ትልቅ የዓሳ ነባሪ አስከሬን አግኝተዋል።

ይህን የዓሳ ነባሪ አስከሬን ለመጠጋት ሽታው ከፍተኛ ፈተና የነበረ ቢሆንም እንደምንም ተጠጉት።

ዓሳ ነባሪው በውስጡ ትልቅ በረከት ይዞ ነበር። ለሽቶ መቀመሚያ በጣም ተፈላጊ የሆነውን 'አምበርግሪስ' የተሰኘውን ንጥረ ነገር ነበር ዓሳ ነባሪው በሆዱ ይዟል። እናም ይህንን ንጥረ ነገር በ1.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመሸጥ ዓሳ አስጋሪዎቹ ሕይወታቸውን ቀይረዋል።