ከሙዚቃዋ የሚገኝ ገቢን ለሴቶችና ለህጻናትን ያበረከተችው ድምፃዊት ሳምራዊት አሰፋ

ታትሟል

አሜሪካ ካሊፎርኒያ ውስጥ ሙዚቃ ይተማረችውና የሙዚቃ መምህርቷ ሳምራዊት አሰፋ 'ሴት' የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም አሰናድታለች። ከአሁን በፊት ነጠላ ዜማዎችንም ለሕዝብ አቅርባለች።

አዲሱ አልበምን ወደኢትዮጵያ ተመልሳ ከሌሎች ሙዚቀኞች ጋር የመጫወት ፍላጎት አላት። አሁን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ይህን ማድረግ ባትችልም በበይነ መረብ የሙዚቃ ድግስ ለማዘጋጀት ሐሳብ ላይ መሆኗን ነግራናለች።

የአዲሱ አልበም ሽያጭ ገቢም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ለሚደርስባቸው ሴቶችና ህጻናት ይውላል ብላለች።