ዐይነ ስውርነት ሕልሙን ከመኖር ያላገደው ጁሊየስ

ታትሟል

ሕልሙን ከመኖር ዐይነ ስውርነት ያላገደው ጁሊየስ። ኬንያዊው ጁሊየስ በ10 ዓመቱ ነው እይታውን ያጣው። በልጅነቱ መኪና ማሽከርከር እና የጥበብ ሥራዎችን ማከናወን ዋነኛ የሕይወት ሕልሙ ነበር። አንድ ቀን ከእንቅልፉ ሲነሳ ግን ራሱን ጨለማ ውስጥ አገኘው። እይታውን ማጣቱ ስጋት ቢፈጥርበትም ሕልሙን ከመኖር ግን አላገደውም።