ትግራይ፡ የአካል ጉዳተኛ ሆኖ ከሞት ያመለጠው ኮሎኔል ሲሳይ

ታትሟል

ኮሎኔል ሲሳይ የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም ጥቅምት 24፣ 2013 ዓ.ም በተቀሰቀሰው የትግራይ ጦርነት ከሚኖርበት ሑመራ ከተማ ከጥቃት አምልጦ ወደ ሱዳን መሻገሩን ተናግሯል። በወቅቱም ብዙ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ገጥመውት እንደነበር ያስታውሳል።