በአይኤስ የፈረሱባቸውን የእምነት ቤቶች በጋራ እየጠገኑ ያሉት የኢራቅ ሙስሊምና ክርስቲያኖች

ታትሟል

የኢራቋ ሞሱል ከተማ ሙስሊም እና ክርስቲያኖችን አቅፋ የያዘች ከተማ ነበረች። ነገር ግን አይኤስ በከፈተው ጥቃት ወደ ፍርስራሽነት ተቀይራለች።

በዚህ ምክንያትም በሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊምና ክርስቲያኖች ከተማዋን ለቀው ተሰደዱ። አሁን ጦርነቱ ሲቆም ከተማቸውን ወደ ነበረችበት ዳግም ለመመለስ በጋራ እየጣሩ ነው።