ከመንግሥት መግለጫ ጀርባ ያለው የሶማሊያ ኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር እውነታ ሲፈተሽ

ታትሟል

በሶማሊያ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ100 በታች መሆኑን መንግስት ይፋ አድርጓል። በመዲናዋ ሞቃዲሾ የሚገኙ የመቃብር ስፍራዎች ግን ኮሮናቫይረስ መከሰቱን ተከትሎ በፍጥነት እየሞሉ ነው። የመቃብር ቆፋሪዎቹም በአንድ የመቃብር ስፍራ ብቻ ባለፉት ጥቂት ወራት ከ2000 ሰው በላይ ሰው መሞቱን ይናገራሉ። ቢቢሲ አፍሪካ አይ በስፍራው በመገኘት ያለውን እውነታ ፈትሿል።