ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በ50 ዓመት ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል
ታትሟል
በመላው ዓለም የኮሮናቫይረስን መከሰት ተከትሎ እንቅስቃሴዎች በአብዛኛው ዝግ ተደርገዋል። በዚህም ምክንያት የምጣኔ ሃብት ቀውስ በብዙ አገራት ዘንድ እየተከሰተ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት መረጃ እንደሚያሳየው እስከ 50 ሚሊዮን የሚሆን የዓለም ሕዝብ እጅግ በከፋ ድህነት ውስጥ ይወድቃል ተብሎ ተሰግቷል።
ይህም በአጠቃላይ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ባለፉት 50 ዓመት የዓለም ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የምግብ እጥረት ሊያጋጥም ይችላል ተብሎ ተገምቷል።