ኮሮናቫይረስ፡ ታካሚዎችን ከመርዳት ያልቦዘኑት የ98 ዓመቱ ፈረንሳያዊ ሃኪም

ታትሟል

የ98 ዓመቱ የእድሜ ባለጸጋ ፈረንሳያዊ ሃኪም አሁንም ህክምና እየሰጡ ነው። ዶ/ር ክርስቲያን ቼናይ እድሜያቸው መግፋቱ ለኮሮናቫይረስ የበለጠ ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው ቢያውቁም 'እኔ ካልረዳኋቸው ማንም የላቸውም' በማለት በአረጋዊያን የእንክብካቤ ማዕከላት ሁሉ በመሄድ ህክምና እየሰጡ ይገኛሉ።