ኮሮናቫይረስ፡ ቬትናም በኮቪድ-19 አንድም ሞት ያላስመዘገበችበት ሚስጥር ምንድን ነው?

ታትሟል

ከቻይና ቀጥሎ የኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው አገራት መካከል ቬትናም አንዷ ነች። በቬትናም ቫይረሱ የተገኘው በጥር ወር አጋማሽ አካባቢ ሲሆን ይህም በአሜሪካም ሆነ በአውሮፓ ከመታየቱ በፊት ነው።

ይሁንና ቫይረሱ እንደሌሎቹ አገራት ሁሉ የሰው ሕይወት መቅጠፍና እንደልብ የመስፋፋት እድል በቬትናም አላገኘም። አንድም ሰው ያልሞተባት ቬትናም በቫይረሱ የተያዙ ዜጎቿም ከ300 ያልበለጡ ሲሆን አብዛኛዎቹም አገግመው ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። ለመሆኑ ቬትናም ምን የተለየ ሥራ ብትሰራ ነው የቫይረሱን ስርጭትና የሚያስከትለውን ሞት መቆጣጠር የቻለችው?