ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኮሮናቫይረስ፡ ጂቡቲ ከአፍሪካ ዘጠነኛዋ የኮሮናቫይረስ ተጠቂ አገር ሆነች
ታትሟል
አንድ ሚሊዮን የማይሞላ ሕዝብ ያላት ጂቡቲ በአፍሪካ ደረጃ በርካታ ታማሚዎችን በማስተናገድ ዘጠነኛ ሆናለች። እስከ ሚዚያ 11 ድረስም በጂቡቲ ቢያንስ 846 ሰዎች በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች መኖራቸው ተረጋግጧል። ከጂቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ሰዎችም ቫይረሱ እየተገኘባቸው ሲሆን እስከ ሚያዚያ 12 ድረስ አምስት ኢትዮጵያዊያን ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።