ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚያበቃው መቼ ነው?

ታትሟል

በቻይና ዉሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስድስት ወራት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ በመላው ዓለም ተሰራጭቷል። ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ሰዎች ደግሞ ለሞት ተዳርገዋል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ የመላው ዓለም ጥያቄ 'ይህ ወረርሽኝ መቼ ያበቃ ይሆን?' የሚለው ነው። ብዙ ተስፋ ሰጪ ነገሮች እየተሰሩ ነው፤ ግን እስከመቼ በተስፋ ብቻ?