ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኮሮናቫይረስ፡ ሦስት ወራትን ዝግ ሆና የቆየችው የውሃን ከተማ ነዋሪዎች ምን ይላሉ?
ታትሟል
በጥር ወር መጀመሪያ የ11 ሚሊዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው የቻይናዋ ዉሃን ከተማ መውጫ በሮቿ ሲዘጋጉና ነዋሪዎች ከቤት እንዳይወጡ እገዳ ሲጣልባቸው፣ ከ7 ቢሊዮን በላይ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ ጉድ ብሎ ነበር። ጊዜ ደጉ ሁሉን ያሳያል እንዲሉ ከሦስት ወራት በኋላ ደግሞ ነገሮች በተቃራኒው መፈጸም ጀምረዋል።
ቀሪው ዓለም በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቤቱን ቆላልፎ ሲቀመጥና ሲጨነቅ ዉሃኖች ከቤታቸው ወጥተው ወደ መደበኛ ሥራቸው እየተመለሱ ነው። በሦስት ወራት የቤት ውስጥ ቆይታቸው ዉሃኖች ብዙ ገጠመኞችን አስተናግደዋል። ገጠመኞቻቸውን ለዓለም ሕዝብ በዚህ መልኩ አካፍለዋል።