ተጨማሪ 1ሺህ 136 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል
ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 1ሺህ 136 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል.
ለ14ሺህ 815 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን 1ሺህ 136 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በሌላ በኩል 888 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ 16 ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው አልፏል።
ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በመላው ዓለም ከ27 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 891,000 ያህሉ ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል። አሜሪካ አሁንም ከዓለማችን አገራት ሁሉ በከፍተኛ ቁጥር በቫይረሱ የተጠቃች ስትሆን በዓለም ላይ ካለው የኮቪድ-19 ቁጥር አምስት እጁ በአሜሪካ ይገኛል ተብሏል። ሕንድ ብራዚል ይዛው የነበረውን ሁለተኝነት በመረከብ በቫይረሱ በከፍተኛ ከተጠቁ አገራት ተርታ በሁለተኛነት ተመድባለች። በሕንድ በቀን 75,000 ሰዎች በኮቪድ መያዛቸው ሪፖርት ይደረጋል። በኢትዮጵያም እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲመረመሩ ከእነዚህም መካከል 59 ሺህ 648 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ባለፉት 24 ሰዓታት ተጨማሪ 1ሺህ 136 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል.
ለ14ሺህ 815 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን 1ሺህ 136 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።
በሌላ በኩል 888 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ 16 ሰዎች ከበሽታው ጋር በተያያዘ ሕይወታቸው አልፏል።
የቻይና ገዥው ፓርቲ በህዝቡ ላይ አንዣቦ የነበረውን ጦርነት ያሉትን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የመከቱትን የጦር ጀግኖች ያለቻቸውን የጤና ባለሙያዎቿን ትልቅ ዝግጅት በማድረግ ክብር ሰጥታለች፤ ሽልማቸዋለች።
የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ሺንፒንግ እንዳሉት ወረርሽኙ ከተከሰተባት እለት ጀምሮ በአለም ላይ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ታድገዋል።
ለዚህም ተግባራቸው ምስጋናን ችረዋቸዋል።
ቻይና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ በመጀመሪያ ደብቃ ቆይታለች በሚል በአንዳንድ አካላት ተተችታለች። አውስትራሊያም የኮሮናቫይረስ አመጣጥን አስመልክቶ ለሚያጣራ ቡድን ድጋፍ ሰጥታለች።
በዚህ የሽልማት ፕሮግራም ላይ ስለ ኮሮናቫይረሱ መንግሥትን በማስጠንቀቁ ቅጣት የደረሰበት ዶክተር ሊ ዌኒላንግም ስሙ አልተጠቀሰም። በኋላም በኮሮናቫይረስ ህይወቱ ማለፉ የሚታወስ ነው።
የኮሮናቫይረስ መነሻ የሆነችው ቻይና ከሞላ ጎደል ህይወት እንደቀደመው ቀጥሏል። ባለፈው ወር በሺዎች የሚቆጠሩ ግለሰቦችም በውሃን በሚገኝ የመዋኛ ገንዳ ፓርቲ ላይ ተሰባስበውም ታይተዋል። በውሃን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የሉም።
እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ መረጃ ከሆነ በመላው ዓለም ከ27 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ 891,000 ያህሉ ደግሞ ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን አጥተዋል።
አሜሪካ አሁንም ከዓለማችን አገራት ሁሉ በከፍተኛ ቁጥር በቫይረሱ የተጠቃች ስትሆን በዓለም ላይ ካለው የኮቪድ-19 ቁጥር አምስት እጁ በአሜሪካ ይገኛል ተብሏል።
ሕንድ ብራዚል ይዛው የነበረውን ሁለተኝነት በመረከብ በቫይረሱ በከፍተኛ ከተጠቁ አገራት ተርታ በሁለተኛነት ተመድባለች። በሕንድ በቀን 75,000 ሰዎች በኮቪድ መያዛቸው ሪፖርት ይደረጋል።
በኢትዮጵያም እስካሁን ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲመረመሩ ከእነዚህም መካከል 59 ሺህ 648 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
የቫይረሱን ስርጭት ባለበት ለመግታት በሕክምና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ምክር መተግበር አማራጭ የሌለው መፍትሄ መሆኑን ባለሙያዎች ዛሬም አበክረው ይመክራሉ።
የቢቢሲን ከኮሮናቫይረስ ጋር የተያያዘ ዘገባ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ እዚህ ይከታተሉ።