ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አውሮፓ በአስርት ዓመታት ውስጥ ባልታየ የከፋ ድርቅ እየተሰቃየች ነው
አውሮፓ በአስርት ዓመታት ውስጥ ባልታየ የከፋ ድርቅ እየተሰቃየች ነው
ታትሟል
የአየር ንብረት ተመራማሪዎች ድርቅ፣ የሙቀት መጠን መጨመር እና ሰደድ እሳትን የመሳሰሉት ከባድ የአየር ሁኔታዎች እየጨመሩ መምጣታቸውን እያስጠነቀቁ ነው።
በዚህም አብዛኛው የአውሮፓ ክፍል ከፍተኛ የሚባል የሙቀት መጠን አስመዝግቧል። በእንግሊዝ ወንዞች እየደረቁ ሲሆን ፈረንሳይ ከ7 ሺህ ሄክታር በላይ ደን በሰደድ እሳት ወድሞባታል።
ስፔንም የውሃ መጠኗ ከ40 በመቶ በታች መውረዱን ገልጻለች። ይህ ሁኔታ መላዋን አውሮፓ አስጨንቋል።
በዚህ ቪዲዮ በአውሮፓ ድርቅ ምክንያት የተስተዋሉ ዋና ዋና ክስተቶችን ያስቃኛል።