ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ለ28 ዓመታት በባቱ ሐይቅ ገሊላ ደሴት ብቻቸውን የኖሩት አዛውንት
ለ28 ዓመታት በባቱ ሐይቅ ገሊላ ደሴት ብቻቸውን የኖሩት አዛውንት
ታትሟል
ወ/ሮ ኩሼ ጎንዶር ትዳር የመሰረቱት በ15 ዓመታቸው በባቱ ሐይቅ ገሊላ ደሴት ነው። ሦስት ልጆች ወልደዋል። ልጆቻቸው አካባቢውን ለቅቀው ሌላ ቦታ መኖር ጀምረዋል።
ጎረቤቶቻቸውም ከደሴቲቱ ወጥተው ከተማ ቢገቡም ወ/ሮ ኩሼ ግን ከደሴቷ አልወጣም ብለው ብቻቸውን እየኖሩ ነው።
ጎረቤቶቻቸውም ልጆቻቸውም በሌሉበት ያለፉትን 28 ዓመታት ወ/ሮ ኩሼ በደሴቷ ብቻቸውን አሳልፈዋል።
ወደፊትም ከደሴቷ የመውጣት እቅድ የላቸውም።