የመጀመሪያው በገመድ ላይ መረማመድ የዓለም ሻምፒዮና ተካሄደ

የመጀመሪያው በገመድ ላይ መረማመድ የዓለም ሻምፒዮና ተካሄደ
ታትሟል

በስዊትዘርላንድ የአልፕስ ተራራ ላይ ከመላው ዓለም የተወጣጡ ተወዳዳሪዎች ተሰባስበው የመጀመሪያውን በገመድ ላይ መረማመድ ሻምፒዮና አካሂደዋል።

ከባሕር ወለል በላይ 2252 ሜትር ከፍታ ባለው የተወጠረ ገመድ ላይ በመረማመድ 31 ተወዳዳሪዎች ችሎታቸውን አሳይተዋል።

በእዚህ ውድድርም በዓለም የመጀመሪያው ሻምፒዮና ለመሆን በፍጥነት መራመድን እና ትርኢት ማሳየትን ጨምሮ አስደናቂ ክንውኖች ተካሂደውበታል።