ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
የላባቸውን ዋጋ ተነጥቀው ቤሩት ጎዳና ላይ የወደቁት ኢትዮጵያውያን
ታትሟል
በኮሮናቫይረስ ምክንያት በሊባኖስ የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ያመጣው የምጣኔ ሃብት ቀውስ ጦሱ ለኢትዮጵያዊያን ተርፏል። በሊባኖስ በቤት ሰራተኛነት የሚሰሩ ኢትዮጵያዊያን በዚሁ ምክንያት አሰሪዎቻቸው ያለምንም ክፍያ አባረዋቸው ሜዳ ላይ ተበትነዋል። ወደ አገራቸው መመለስ ቢፈልጉም የአውሮፕላን በረራ በመቋረጡ የሚሄዱበት ግራ ገብቷቸዋል። በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ በር ላይ ተሰባስበው ችግራቸውን ለቆንስላው ቢገልጹም እስካሁን መልስ አለማግኘታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።