ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
"ከየካቲት እስከ ሰኔ ድረስ በረራ በመከልከሉ 1 ቢሊዮን ዶላር አጥተናል"
ታትሟል
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በአየር ትራንስፖርት ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ጫናን ማሳረፉን ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንዳጣ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ገልፀዋል።
የኮሮናቫይረስ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ በአየር መንገዶች ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ቀውስ ማምጣቱን እንዲሁም ከ90 በመቶ በላይ የመንገደኛ በረራዎች መቆማቸውን ለቢቢሲ የተናገሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፣ ያንን ተከትሎ ደግሞ ከየካቲት እስከ ሰኔ መጨረሻ ድርጅቱ መንገደኛ በማጓጓዝ ሊያገኘው ይገባ የነበረው ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ገቢ ሳያገኝ መቅረቱን ገልፀዋል