ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ኮሮናቫይረስ፡ ኮሮናቫይረስ እና ጥይት በኬንያ
ታትሟል
በኬንያ መዲና ናይሮቢ ማታሬ ተብሎ የሚጠራው ሰፈር እጅግ በተጎሳቆለ ሁኔታ እሰከ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች የሚኖሩበት አካባቢ ነው።
የኮሮናቫይረስ መከሰትን ተከትሎ የማታሬ ነዋሪዎች ፈተናቸው አይሏል። በአገሪቱ የታወጀውን የሰዓት እላፊ ለማስፈጸም ፖሊስ የጭካኔ በትሩን እያሳረፈባቸው ነው። በአካባቢው ሰዓት እላፊውን ለማስፈጸም በሚል የ13 ዓመት ልጅ በፖሊስ ጥይት ተመቶ ሞቷል። ሌላም ሰው እንዲሁ ሞቶ ተገኝቷል። የአካባቢው ነዋሪዎች መንግሥትም ኮሮናም እኩል እየገደሉን ነው ይላሉ።