ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
ቀባሪን ያጡትን አለሁላችሁ ያለው ብራዚላዊው አስከሬን ሰብሳቢ
ታትሟል
በአሁኑ ወቅት ብራዚል የኮሮናቫይረስ ማዕከል ከሆኑ አገራት መካከል አንዷ ሆናለች። በየቀኑ የሟቾች ቁጥርም በአማካይ ከአንድ ሺህ በላይ እየሆነ ነው።
የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ አስከሬን ቀባሪ እያጣ ነው። ከተማቸውን ንጹህ ለማድረግ ታዲያ በጎ አድራጊ የቀብር አስፈጻሚዎች በከተሞች ተሰማርተው በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሞቱ ሰዎችን አስከሬን በመሰብሰብ እየቀበሩ ነው።
የቀድሞው የታክሲ ሾፌር ጁራሲም በዚሁ በጎ አድራጊነት ተሰማርቶ ማናውስ በተባለች የብራዚል ከተማ ከ1400 በላይ በኮሮናቫይረስ የሞቱ ሰዎችን ቀብሯል።