ይህ ዝቅተኛ ዳታን በመጠቀም ጽሑፍ ብቻ የሚቀርብበት የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽ ነው
አንድ ፎቶ ዝነኛ ያደረጋት አይናፋሯ ሕንዳዊት ታዳጊ
ታትሟል
ሃይድርባድ የተሰኘችው የደቡባዊ ሕንድ ግዛት ነዋሪ የሆነችው የአምስት ዓመቷ ሕፃን ፎቶ ሰሞኑን የሃገሬውን ሰው ጉድ አሰኝቷል። ፎቶው ይህች ሕፃን ትምህርት ገበታ ላይ ያሉ እኩዮችዋን ከውጪ አጮልቃ ስትመለከት ያሳያል። ይህ ፎቶ ቴሉጉ በተሰኘው ጋዜጣ የፊት ገፅ ላይ ከወጣ ወዲህ መነጋገሪያ ሆነ። ርዕሱ ደግሞ "የተጠማ ዕይታ" ይላል።